image
image
image
image
image

በክፍለ ከተማው ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሰው ተኮር የልማት ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ - ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ

ህዳር 4, 2018
በልደታ ክ/ከተማ ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሰው ተኮር የልማት ስራዎች በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥሉ የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ ገለጹ። በክ/ከተማው በግንባታ ላይ የሚገኙ፣ የተጠናቀቁና አዳዲስ ሰው ተኮር እና የኢንሼቲቭ ስራዎችን ከምክር ቤት አባላት፣ ከመንግስት ሰራተኞች፣ ተፅኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና በጎ የማህበረሰብ አንቂዎች የተውጣጣ ቡድን በመዘዋወር የመስክ ምልከታ አድርገዋል። የተከናወኑ የሰው ተኮር እና በኢንሼቲቭ የተሰሩ ልማት ስራዎች አስደናቂ ውጤት የተገኘባቸው መሆኑን ወ/ሮ ልዕልቲ ገልጸዋል። የኢንሼቲቭ ስራዎቹ በተያዘላቸው እቅድ መሠረት መቀጠላቸውን ያነሱት ደግሞ የክ/ከተማው ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ አራርሳ ድሪባ ናቸው። አቶ አራርሳ አያይዘው በመስክ ምልከታው የግንባታ ስራቸው የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች አገልግሎት እየሰጡ መሆኑንና በስራ ላይ ያሉትም በጥራትና ፍጥነት እየተከናወኑ መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል። አዳዲስ የኢንሼቲቭ ፕሮጀክቶች እና የዝግጅት ምዕራፍ ስራዎች እንዲሁም ነባር ፕሮጀክቶች በተቀመጠላቸው ጊዜ በጥራት እየተከናወኑ መሆኑን ያረጋግጥንበት ነው ሲሉ የጉብኝቱ ተሳታፊዎች ተናግረዋል። በክ/ከተማው ህዝቡን በማሳተፍ የሚከናወኑ የልማት ስራዎች በተጠናከረ መልኩ እየቀጠሉ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ባለሃብቱንና ህብረተሰቡን በማስተባበር 58 የሚሆኑ የኢንሼቲቭ ስራዎች መሰራታቸውን በጉብኝቱ ወቅት ማየት ተችሏል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች