#

አቶ መቅድም ገ/ሃና
የአየር ንብረት ለውጥ ቡድን መሪ

28 Oct 2025

የቡድን መሪዉ መልዕክት

ሀገራችንን መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ተርታ ለማሰለፍ፣ ዜጎች በምቹና ተስማሚ አካባቢ የመኖር መብታቸውን እውን ለማድረግ እንዲሁም ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂን ተግባራዊ ለማድረግ የአካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች በመንግሥት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ይገኛል፡፡ነገር ግን ከተማችን ለአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ይበልጥ ተጋላጭ ሆናለች፡፡ ለዚህም መገላጫው ወደ ከተማዋ አየር የሚለቀቁት የሙቀት አማቂ ጋዞች መጨመርና ለመቀነስ የሚደረገው ጥረት አናሳ መሆን ለጎርፍ አደጋና የአየር ሙቀት መጨመር ምክንያት ሆኗል ፡፡ ማንኛወም የልማት ፕሮጀክቶች ወደ ትግበራ ከመግባታቸው በፊት በአካባቢ ላይ የሚያደርሱት አሉታዎ ተፅዕኖ አስቀድሞ ሳይገመገሙ በስፋት ወደ ስራ በመግባታቸው በከተማዋ አካባቢ ላይ ተጨማሪ ጉዳት ከማስከተላቸውም በተጨማሪ አካባቢና ልማት ተጣጥመው እንዳይሄዱ ምክንያት ሆኗል፡፡ በከተማ ደረጃ የታዳሽ ሃይል አጠቃቀምና አማራጭ የኢነርጂ ቴክኖሎጂዎችን ስርዓት መዘርጋት ፤ማስፋት፤ ማስረፅና ማጎልበት ባለመቻሉ በአየር ብክለት፤ በደን ኃብት እና በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ተፅዕኖ በማሳደር ላይ ይገኛል፤በመዲናችን አዲስ አበባ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የአየር ንብረት ለውጥ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ፣ በመልም አስተዳደር ዘርፎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል፡፡ የሙቀት መጠን በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር፣ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ መዝነብ፣ የጎርፍ አደጋ መከሰት በሰዎችና በንብረት ላይ የከፋ ጉዳት በማድረስ ፣በሰዎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ላይ ተፅኖ እየፈጠረ ይገኛል፡፡ ይህም ሁኔታ በዚህ መንገድ ከቀጠለ በአሁኑ ትውልድ ብቻ ሳይሆን በቀጣዩ ትውልድ ላይ ተፅዕኖ መፍጠሩ አይቀርም፡፡ ምክንያቱም ችግር እየተስፋፋና በመጠንም እየጨመረ ሲመጣ በሰው ልጅ ጤንነት ላይ በተለይም በህፃናት የመተንፈሻ አካላት እና በአይምሮ ላይ የከፋ ጉዳት ስለሚያደርስ ነው፡፡

ይህንን ለመቋቋም የኢፊዲሪ መንግስት የችግሩ አሳሳቢነትና አንገብጋቢነት በመረዳት ይህንን ተግባር ውጤታማ በሆነ መልኩ በመምራት ችግሩን ለመቀልበስ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ተቋም መዋቅር በየደረጃው በአዋጅ ቁጥር 74/2ዐ14 መሰረት እንዲቋቋም ተደርጓል፡፡ልደታ ክፍለ ከተማ አካባቢ ጥበቃ በዚሁ መሰረት የተቋቋመ ነዉ፤በዚህ ጊዜ እየተሰሩ ካሉ መልካም ጅምር ስራዎች በተጨማሪ የሁላችንም ድርሻ እና ትግባራዊ እንቅስቃሴ የሚፈልጉ አሉ ፡፡ ለአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ተጋላጭ የህበረተስብ ክፍሎች ድጋፍና ክትትል ማድረግተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች እንዲለዩና የተጋላጭነት ደረጃና ለመቋቋም ያላቸው አቅም ማወቅ፣ለአየር ንብረት ለውጥ በየሴክተሩ አሃድ ማቋቋምን፣ ከየአሃዱ ለተውጣጡ ስልጠና መስጠትን፣ ሴክተሮች እቅድ እንዲያዘጋጁ ለመደገፍ ፣ ምርጥ ተሞክሮ እንዲለዋወጡ ማድረግን ልናተኩርባቸዉ ይገባል፡፡

የኢነርጂ ቴክኖሎጂዎችን የዲዛይንና የፕሮሞሽን ስራ በመስራት ለተጠቃሚዎች በማስፋፋት፣ በኢነርጂ ቴክኖሎጂዎች ዓይነትና አጠቃቀም በቂ ግንዛቤ በመስጠት ፣በማገዶ አጠቃቀም ምክንያት በአካባቢ ላይ እየደረሰ ያለዉን ጫና ለመቀነስ የፀሃይ፣የነፋስ፣የጂኦተርማልና የአነስተኛ ሃይድሮፓወር የአማራጭ ኢነርጂ ቶክኖሎጂዎችን ማጥናት፣ማስፋፋትም ልዩ ትኩረት ይሻል፡፡ መልዕክቴን ለማጠቃለል ያህል የአየር ንብረት ለውጡን መቋቋም የሚችል የሕብረተሰብ ክፍል ለመፍጠር፣በአማራጭ ኢነርጂ አቅርቦት የረካ ህብረተሰብ፣በደን ላይ የሚደርስ ጫና ለመቀነስ፣የግልፀኝነትና ተጠያቂነትን መርህ የተከተለ ለኢኮኖሚ፣ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ልማት ምቹ የሆነ አካባቢና የአየር ንብረት ለዉጥ የማይበገር አርንጓዴ ልማት በመተግበር ለክፍለ ከተማችን ማህበረሰብ ለኑሮ ተሰማሚ የአርንጓዴ ልማት በክፍለ ከተማዉ ማስተር ፕላን መሰረት ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ጉልህ ሚና መጫወት የሁላችንም ድርሻ እንዲሆን አደራ ለማለት እወዳለሁ፡፡

በቡድኑ የሚሰጡ የአገልግሎት አይነቶች

የኢነርጂ ቴክኖሎጂና ምንጮች ላይ የግንዛቤ ስልጠና መስጠት፣

ከተገልጋይ የሚጠበቅ ቅድመ ሁኔታ

  በአካል ተገኝቶ መሳተፍ

የኢነርጂ ምንጮችና ቴክኖሎጂዎችን የተመለከቱ የግንዛቤ ትምህርት መስጠት፣

ከተገልጋይ የሚጠበቅ ቅድመ ሁኔታ

በአካል ተገኝቶ መሳተፍ

የኢነርጂ ቴክኖሎጂና ምንጮች አጠቃቀምና አመራረት ስልጠናዎችን ማዘጋጀትና መስጠት ፣

ከተገልጋይ የሚጠበቅ ቅድመ ሁኔታ

በአካል ተገኝቶ መሳተፍ

የኢነርጂ ምንጮችና ቴክኖሎጂዎችን የማስተዋወቅና አጠቃቀሙን የማስረጽ ስራ መስራት

ከተገልጋይ የሚጠበቅ ቅድመ ሁኔታ

በአካል ተገኝቶ መሳተፍ

መልዕክትዎን ይላኩ