በልደታ ክ/ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ዋና ዋና አገልግሎቶች
- 1. በአካባቢ ብክለት እና ተጽእኖ ግምገማ ቡድን የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች
- ስለአካባቢ ብክለት፣ህጎችና የአፈፃፀም መመሪያዎች ለህብረተሰቡ ስልጠናና ግንዛቤ መስጠት
- ብክለት በሚያደርሱ ተቋማት ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ ፣
- የብክለት መጠን በመለካት እርምጃ መውሰድ ፣
- የፕሮጀክቶችን የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ሰነዶችን በመገምገምና መቆጣጠር የማስተካከያ ሀሳብ መስጠት
- የአካባቢ አያያዝ ዕቅድ እና የአካባቢ ተፅእኖ ክዋኔ ሪፖርት መከታተል
- 2. በአየር ንብረት ለውጥ ቡድን የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች
- ስለአየር ንብረት ለውጥ፣ ህጎችና የአፈፃፀም መመሪያዎች ለህብረተሰቡ ስልጠናና ግንዛቤ መስጠት፣
- ለአየር ንብረት ለውጥን በዘርፍ መ/ቤቶች በዕቅድ መካተቱን ማረጋገጥ ፣
- ለአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ተጋላጭ የህበረተስብ ክፍሎች ድጋፍና ክትትል ፣
- የኢነርጂ ቴክኖሎጂዎችን የዲዛይንና የፕሮሞሽን ስራ በመስራት ለተጠቃሚዎች ማስፋፋት፥
- 3. በስርዓተ ምህዳርና ብዝሃ ህይወት አጠቃቀም እና ቁጥጥር ቡድን ስር የሚሰጡ አገልግሎቶች
- በፕላን ለአረንጓዴነት የተመላከቱ ቦታዎች ከህገ ወጥ ወረራ ስለመጠበቃቸው እና ለታለመላቸው ዓላማ መዋላቸውን የቁጥጥር ስራዎችን ይሰራል፤
- የአንጓዴ ቦታዎች ከወራሪ አረሞች፣ ከእጽዋት በሽታዎች እና ተባዮች መጠበቃቸውን በዳሰሳ ጥናት በመለየት የቁጥጥርና የክትትል ስራችዎችን ይሰራል፤
- በክፍለ ከተማችን በአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር በየዓመቱ የሚተከሉ ችግኞችን የጽድቀት መጠን ዳሰሳ ጥናቶችን በመስራት ግኝቱንና ውጤቱን ለከተማ ውበት ጽ/ቤት እና ለአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ያሳውቃል፤ በግኝቱ መሰረት የማስተካከያ እርምጃዎች መወሰዳቸውንም ይከታተላል፤
- በዘርፉ ለተመረቁ እና በአረንጓዴ ልማት ስራዎች ላይ የማማከር አገልግሎት መሰጠት ለሚፈልጉ ባለሙያዎች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ይሰጣል፤
- በአፈር መሸርሸር እና መከላት ምክንያት የተጎዱ ቦታዎችን በመለየት የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች እንዲደረጉ ለሚመለከተው አካል በሪፖርት ያውቃል ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፤
- በግል፣ በመንግስት፣ በማህበራትና በተቋማት ይዞታዎች ላይ የተተከሉ ዛፎች ለምርት ሲደርሱ፣ በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ሲያደርሱ፣ ከመብራት ጋር ንክኪ ሲፈጥሩ እና መሰረተ ልማት የሚያበላሹ መሆናቸው በባለሙያ ከተረጋገጠ የቆረጣ እና የምልመላ ፈቃድ ይሰጣል፤
- ለዛፍ ቆረጣ ከሚሰጥ ፈቃድ ላይ የሮያሊቲ ክፍያ ብር ገቢ በማሰባሰብ የመንግስትን ገቢ በማሳደግ ረገድ እና ደኖች ያላቸውን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ በመጨመር ስራዎችን ይሰራል፡፡
- ስለ አካባቢ ጉዳዮች የህብረተሰቡን ተሳትፎ ለማሳደግ የተለያዩ የግንዛቤ ስራዎችን ይሰራል፤